Steel Raw Materials and Products
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ ቋሚ ንብረቶችን የተማሪ የብረት አልጋዎች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የተማሪ ወንበሮች እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Steel Raw Materials and ProductsSteel, Metals and AluminiumEquipment and Accessories
Addis Ababa
More tags
Electrical, Electromechanical and ElectronicsOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesComputer and AccessoriesIT and TelecomHouse FurnitureFurniture and FurnishingOffice FurnitureOther SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal SaleMetal and Metal WorkingWood and Wood WorkingOther MetalsAmharic2merkatoበኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ
Description
ያገለገሉ እቃዎች የጨረታሰነድ 001/2018
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ የመንግስት ቋሚ ንብረቶችን የተማሪ የብረት አልጋዎች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን የተማሪ ወንበሮች እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
- ተጫራቾች ለ2018 ዓ/ም ከዘርፉ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ብቻ Min/of/beherawi /ha/ma/ma/ swers/liz ስም በተከፈተ በኢት/ያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000554811454 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይስ በማምጣት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ንብረቶቹን በማንኛውም የመንግስት የሥራ ሰዓት በኮሌጁ ግቢ ውስጥ በአካል መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የንብረቱንጠቅላላ ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅታችሁም ህጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ አድርገው ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢ/ያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ ውስጥ በሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዝብ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ጨረታው ሳይከፈት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሽናፊ ከታወቀ ወዲያውኑ ለተሸናፊዎች የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ድርጅት ንብረቶቹን ጨርሶ ሲያነሳ የሚመለስለት ይሆናል።
- አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በአጠቃላይ የማንሳት ግዴታ አለበት።
- ኮሌጁ ለአፈፃፀም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ ሞጆ በቀጥታ ስልክ ቁጥር-0221162424 ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎችን የነጠላ ዋጋ መስጠት አይቻልም። አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ድምር ነው።
- ተጫራቾች የመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ (EGP)ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-26 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T08:59:50.000Z