Construction Machinery and Equipment
የንኮማድ ኮንስትራክሽንኃ/የተ/የግ/ማህበር ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታማስታወቂያ
የንኮማድ ኮንስትራክሽንኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤
በአዲስ አበባ ቦሌ ክሬሸር ሳይት በሚገኘው የዕቃ ግምጃ ቤት ተከማችቶ የሚገኙ ዝርዝራቸው በመጫረቻ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ንብረቶች የኮንስትራክሽን መገልገያ ዕቃዎች፣ ሚክሰር፣ ኮምፓክተር፣ ኮምፕረሰር፣ ቫይብሬተር፣ ተሽከርካሪ፣ ማሽነሪ ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተመለከተው የኩባንያው አድራሻ በመቅረብ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና መጫረት ይቻላል።
የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች፣ ንብረቱ በሚገኝበት በአዲስ አበባ ቦሌ ክሬሸር /ከሰፊራ መስጊድ ወደ አይ.ሲ.ቲ በሚወስደው መንገድ በመገኘት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በመገኘት ዕቃውን መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን በ18/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋው 20% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ ከፍሎ በቀጣዩ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን ንብረት አውጥቶ መውሰድ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያሸነፈበትን ዕቃ ካላወጣ ግን ኩባንያው ኃላፊነቱን አይወስድም።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።”
የንኮማድ ኮንስትራክሸን ኃ/የተ/የግል ማህበር
አድራሻ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ
ዕቃና አገልግሎት ግዥ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107
011 551 4087/ 011 553 3766
የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Bid opening: 2026-08-24 10:00
- Bid opening (note): በ18/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yencomad Construction P.L.C.
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T11:45:52.000Z