Other Sales

የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት የፕላስቲክ ሳጥኖች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የምርጫ ማስፈጸሚያ የፕላስቲክ ሳጥኖችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPS/NVP-1FBI/02/11/2018

የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሆነ ያገለገሉ የምርጫ ማስፈጸሚያ የፕላስቲክ ሳጥኖች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ተጫራች ፕላስቲክን ለመልሶ መጠቀም ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በዘርፉ በቅርብ ፈቃድ የተሰጠው መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ፈቃድ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ 01.0 ቢሮ በመምጣት የንብረቶች ዝርዝር መረጃ፤ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ገቢ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3, ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከኣዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፤ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፤ ይሁንና የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 2 (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 /መቶ ሺህ/ ብር ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

6. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጭራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፤

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፤ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል

8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው

9. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ - በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡

11. ተጫራቾች ያሸነፉትን ፕላስቲኮች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ንብረቱ በሚገኝበት አቅራቢያ ፕሪንት አውት ደረሰኝ ማውጣት በሚቸል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ማንሳት የሚኖርባቸው ሲሆን ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትከክለኛ ኪሎ ግራም መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሃሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የስጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግለት ይሆናል።

12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የኢፌዲሪ የመንግሥት ገዥ አገልገሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ስፊት
ለበለጠ መረጃ የተቋማችንን ድህረ-ገጽ: www.pps.gov.et  ይጎብኙ አዲስ አበባ

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Public Procurement Service
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 /መቶ ሺህ/ ብር ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T08:06:01.000Z
← Back to all tenders