Other Sales
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገለ ጎማ እና ባትሪ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማ እና ባትሪ
መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ ለመሸጥ የመጣ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገለ ጎማ እና ባትሪ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የማክበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
ክፍል አንድ
የተጫራቾች መመሪያ
- ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል።
- ተጫራቾች መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ባሉት የሥራ ቀናት መግዛት ይችላሉ
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት ከ300 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ግቢ (ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ) በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች የተለያዩ ያገለገለ ጎማ እና ባትሪ ዓይነታቸውን መሰረት በማድረግ የሚገዛበትን የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ የሚገዛውን መጠን በማስገባት መጫረት ይኖርበታል።
- የዚህ ጨረታ ከተቀመጠው መነሻ ዋጋ በታች መጫረት አይቻልም። ከመነሻ ዋጋ በታች ያስገቡ ተጫራቾች በቀጥታ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለፅ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።
- ጨረታው ነሀሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ በ4:30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- ለሽያጭ የቀረቡት የእቃዎች ዓይነት የተለያዩ ያገለገለ ጎማ እና ባትሪ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስስክ ቁጥር
011-440-3434
ማዞሪያ 011-442-2270/71/72
E-mail አድራሻ [email protected]
የድህረ ገፅ አድራሻ WWW.dce-etcom
ፖ.ሳ.ቁ 3414/114-40-04-71/0114-42-07-46
የመካላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-25 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T09:41:32.000Z