House Furniture

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር  ሐ- 6 /2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጃ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጪዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም

  • CHILDREN FORCE BABY FROCK & OTHER,
  • LABORATORY STOOL CHAIR COMPLETE SET DOUBLE LEAF STEEL FIRE RATED DOORI PERFUME HAIR CLIPPER,
  • VACUUM FLASK: CHEWING GUM BANANA & CHOCOLATE AS የተለያዩ አልባሳት ጫማዎችና ሌሎች እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃልን።

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,00.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHOPIAN CUSTOMS COMMISSION WODO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ እና ሞጆ ቅርንጫፎች፣ መዘጋጀት አለበት።
  4. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
  5. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል እይቻልም የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  6. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  7. በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ እድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
  8. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
  9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 10:45
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡45 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-19 11:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T11:18:35.000Z
← Back to all tenders