Other Sales

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተወረሱ የተለያዩ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-07/2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጪዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም ጫማና ሽቶዎች፣ HIK VISION SOLID STATE DRIVES, HDD SEAGATE & COMPUTER RAM DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER, AUTOMATIC VOLTAGE REGULATOR & OIL FLTER እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን ሰነድ በመግዛት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት መመልከት ይቻላል።

2) ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ – ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

3) ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎቸ መዘጋጀት አለበት።

4) የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5) ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6) የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7) በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8) አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10) ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡45 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:02:14.000Z
← Back to all tenders