Textile, Garments and Uniforms

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ አዳዲስ አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የእይታ መሣሪያዎች (መነጽር)፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር ግ-04/2018/19 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ አዳዲስ አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የእይታ መሣሪያዎች (መነጽር)፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፦

1. ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው እቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራቾች 100 ብር በመከፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ እቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. በጨረታው የወጡትን ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ በቀበሌ መታወቂያ ብቻ መጫረት ይችላል።

.

 

የእቃው ዓይነት

 

የጨረታው ዓይነት

 

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ስልክ ቁጥር

 

1

አዳዲስ አልባሳት

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

 

 

 

022-111-8429

 

 

 

022-211-8925

 

2

የኤሌክትሮኒክስ

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

3

ኮስሞቲክስ

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

4

ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

5

ሸቀጣሸቀጥ /ልዩ ልዩ እቃዎች

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

6

ኮንስትራክሽን ማቴሪያል

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

7

የእይታ መሣሪያዎች መነጽር

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

8

የቢሮ መገልገያ እቃዎች

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

9

ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

10

የተሽከርካሪ ጐማዎች

ግልጽ

08/12/2018

15/12/2018

4:00

8:00

4. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የእቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

5. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Commission Adama Branch Office) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም። ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

7. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፣ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 / ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55 11/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-21 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ምድብ 5%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:17:48.000Z
← Back to all tenders