Other Sales

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሊንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ሸቀጣሸቀጥ ልዩልዩ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ አዳዲስ አልባሳት፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያል (የቧንቧ እቃዎችን) በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ሐራጅ ጨረታ
ቁፕር 05/2018/19 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሊንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ሸቀጣሸቀጥልዩልዩ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ አዳዲስ አልባሳት፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያል (የቧንቧ እቃዎችን) በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡- በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው ፣ የምስከር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሸን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሸን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

.

የእቃው አይነት

 

የጨረታው አይነት

 

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

 

ጨረታው የሚጀርበት ሰዓት

 

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

 

ስልክ ቁጥር

 

1

ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)

ሐራጅ

08/12/2018

 

13/12/2018

 

4:00

 

8:00

 

022 111 8429/

022 211 8925

2

ኤሌክትሮኒከስ

 

ሐራጅ

08/12/2018

 

13/12/2018

 

4:00

 

8:00

 

022 11 18429/

022 211 8925

3

አዳዲስ አልባሳት

ሐራጅ

 

 

 

 

 

4

ኮስሞቲክስ

 

ሐራጅ

08/12/2018

 

13/12/2018

 

4:00

 

8:00

 

022 111 8429/

022 211 8925

5

የኮንስትራክሽን ማቴሪያል

 

ሐራጅ

08/12/2018

 

13/12/2018

 

4:00

 

8:00

 

0221118429/

022 211 8925

6

የኮንስትራክሽን ማቴሪያል /የቧንቧ ዕቃዎች/

ሐራጅ

08/12/2018

 

13/12/2018

 

4:00

 

8:00

 

022 111 8429/

022 211 8925

4. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።

5. በሐራጅ ጨረታለምትወዳደሩ ለጨረታውዋስትና የሚሆንማለትም፣ ለምድብ 01,ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 77,800.00፤ ለምድብ 02, ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩ) ብር 33.300.00፣ ለምድብ 03, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 191,500.00 ፣ለምድብ 04, ኮስሞቲክስ ብር 406,400.00 ፣ ለምድብ 05, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ብር 213,500.00፣ ለምድብ 06, ኮስሞቲክስ ብር 849,300.00፣ ለምድብ 07, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 203,400.00 ፣ ለምድብ 08, ኮስሞቲክስ ብር 204,500.00፣ ለምድብ 09, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(የቧንባ እቃዎች) ብር 219,400.00 ለምድብ 10, ኤሌክትሮኒክስ ብር 119,100.00፣ ለምድብ 11, ኤሌክትሮኒክስ ብር 73,000.00፣ ለምድብ 12 ኮስሞቲክስ ብር 23,600.00፣ ለምድብ 13, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 127,100.00፣ ለምድብ 14, አዳዲስ አልባሳት ብር 84,000.00፣ ለምድብ 15, አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቅ) ብር 3,915,400.00፣ ለምድብ 16, አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቅ) ብር 1,985,000.00 ለምድብ 17, ኤሌክትሮኒክስ ብር 64,000.00፣ ለምድብ 18, አዳዲስ አልባሳት ብር 16,000.00 እና፣ ለምድብ 19, ኮስሞቲክስ ብር 15,000.00 በ(Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሠራት ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማየት እና መጫረት ይቻላል።

7. በሐራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 / ሶሰት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10 .ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

11. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

NB: በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራች ቢያሸንፍ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።

የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልከ መስመር
09-05-11-55 11/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8426 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): 13/12/2018 4:00 ሰአት (ከተራ ቁጥር 3 በስተቀር)
  • Bid opening: 2026-08-19 14:00
  • Bid opening (note): 13/12/2018 8:00 ሰአት (ከተራ ቁጥር 3 በስተቀር)
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:24:43.000Z
← Back to all tenders