Other Sales

በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው የሚገኙ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፤ የመንገድ ዳር ፖሎች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 1/2019

በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው የሚገኙ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች ፤ የመንገድ ዳር ፖሎች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

1, መስሪያ ቤቱ አድረሻ፤ ሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስቶ ብር/ በመግዛት ከሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ግዥ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

2. ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በግዛት ከሮቤ ከተማ ን/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ በባንክ በተረጋገ ሲፒኦ ብቻ በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች በሮቤ ከተማ ገልማ አባ ገዳ አዳራሽ በመገኘት በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።

7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚው ዕለት 5:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ በሮቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የባንክ አካውንት ላይ ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ንብረት 15 ቀን ውስጥ ማንሳት አለበት።

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

CPO ለማሰራት ሮቤ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፡- 09 34 86 64 74 / 09 12 36 52 94 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ ስራ ቀን ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:31:46.000Z
← Back to all tenders