Other Sales
አከይ ኦንፎ ዴፋቮሪዜ የተባለው አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አከይ ኦንፎ ዴፋቮሪዜ የተባለው አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተጫራቾች
1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት የድርጅቱ ንብረት ባለበት ግቢ በመገኘት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት እና በአስራ አምስተኛው ቀን 7፡30 ሰዓት ድረስ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች መመልከት ይችላል።
2. ተጫራቾች የሚገዙትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
4. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Colum/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በድርጅቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፤ የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
5. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ እና በ7 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ ከድርጀቱ መግዛት ይችላሉ።
7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀነ-8፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግቢ ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 09 11 67 63 13 / 09 55 99 21 87/ 09 39 66 58 04/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ኮተቤ ካራ መሳለሚያ ልዩ ስሙ ዘርፌ ቦኖ መቅደስ ግሮሰሪ ወረድ ብሎ
አከይ ኦንፎ ዴፋቮሪዜ
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 13:30
- Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-31 14:00
- Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: AcEdE
- Buyer address: ኮተቤ መሳለሚያ ዘርፌ ቦኖ አካባቢ
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T08:38:19.000Z