Disposal Sale

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎችና ልዩ ልዩ ዓይነት ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2026/27

1. ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎችና ልዩ ልዩ ዓይነት ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ካለ ወይት የታደሠ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታ ዋጋው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከፈለገ ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ወረድ ብሎ በሚገኘው ግቢ የባንኩ ንብረት ክፍል እና ሜክሲኮ ኬኬር ሕንጻ ፊትለፊት በሚከኘው የባንኩ ንብረት ክፍል በአካል በመቅረብ እቃዎቹን ይችላሉ።

7. ግልጽ ጨረታው ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በእስቱ ጠዋት 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች እቃዎቹ ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት እና እቃዎቹን በአግባቡ ተመልክተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል።

9. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ

ስልክ ቁጥር 011 558 1204 ወይም 011 531 8097 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-01 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Global Bank Ethiopia S.C.
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T13:07:58.000Z
← Back to all tenders