Disposal Sale

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር:ኢኢግ/ንአአኮ/ብግጨ/05/2018

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ንብረትነታቸው የዋና መ/ቤት እና በስሩ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሆኑ በአዲስ አበባ (ሳሪስ፣ ገርጂ፣ ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ እና አዲስ ማሽን ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግቢ፣ መካነሳ፣ አቃቂ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሞጆ እና አዳማ የሚገኙ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር  ይችላሉ፡፡

  1.  በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው ህንፃ ብሎክ ቢ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቀን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የጨረታ መነሻ ዋጋ ከሎት 11-17 እና ከሎት 18-22: የንብረቶቹን ግምታዊ ዋጋ 2% ለተሽከርካሪ፣ ትራክተር እና ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ የንብረቶቹን ግምታዊ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሚሸጠው የጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
  6. ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የመነሻ ዋጋ ከላይ በተራ ቁጥር 4 ላይ የተገለጸውን ያህል መጠን ያልያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀናት ተቆጥሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በጥዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግሩፑ ዋና መ/ቤት ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  8.  የጨረታ ውጤት በግሩፑ ማስታወቅያ ቦርድ ላይ የሚለጠፍ ይሆናል፣
  9.  በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን  10 ፐርሰንት የውል ማስከበርያ CPO በማሰራት የውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውል ስምምነት ካልተፈፀመ ለጨረታ ማስከበርያ የተያዘ CPO ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል፣
  10. ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  11.  አሸናፊ ተጫራቾች የውል ስምምነት በተፈፀመ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን አጠቃላይ ገንዘብ መክፍል ይኖርባቸዋል፡፡ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ካልተከፈለ ለውል ማስከበርያ የተያዘ CPO ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል፣
  12.  አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን ግሩፑ በሚያወጠው ፕሮግራም መሠረት በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  13. ዝርዝር የጨረታ አካሄዱን በተመለከተ ግሩፑ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን
  14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0986333355 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  15. ግሩፑ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ማስታወሻ:-

ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000028606177 ሜክሲኮ ቅርንጫፍ፣ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1014900057975 እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01325662239600 መሰረት ይሆናል፡፡

ከላይ ለተጠቀሰው አድራሻ:

ሻጭ

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

በግሩፑ በኩል የተወከለው

ንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ

የቢሮ ቁጥር

Block-B 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 አዳራሽ

አድራሻ

ሜክሲኮ ከፌደራል ፖሊስ ዋና /ቤት 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

ከተማ//

አዲስ አበባ ሜክሲኮ ልደታ /

አገር

ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር

0986333355

 ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀናት ተቆጥሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀናት ተቆጥሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Engineering Group
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T13:44:49.000Z
← Back to all tenders