Spare Parts and Car Decoration Materials
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ ያገለገሉ የከባድና የቀላል መኪና ጎማዎች፣ ያገለገሉ የከባድና የቀላል መኪና ባትሪዎች፣ ልዩ ልዩ የጣውላ እንጨቶች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ቦንዳዎች ያገለገሉ በርሜሎች እና የውሃ ታንከሮች በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ ያገለገሉ
- ሎት 1. የከባድና የቀላል መኪና ጎማዎች
- ሎት 2. ያገለገሉ የከባድና የቀላል መኪና ባትሪዎች
- ሎት 3. ልዩ ልዩ የጣውላ እንጨቶች
- ሎት 4. ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ቦንዳዎች ያገለገሉ በርሜሎች እና የውሃ ታንከሮች በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. ተጫራቾች ከድርጅቱ ዋና ማስተባበሪያ መ/ቤት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች መግዛት ይችላሉ።
2. ማንኛውም የጨረታ ሰነድ የገዛ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚገዙትን በሎት 1 እና 2 ላይ የተገለጹትን የከባድና የቀላል መኪና ጎማዎች እና ባትሪዎች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሲፒኦ የሚዘጋጀው MENSCHEN FUR MENSCHEN በሚል ስም ነው፡፡ ለሎት 3 እና 4 የሚወዳደሩ በጥቅል 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሁለቱን ሲፒኦ በድምር ወይም በተናጠል ማሰራት ይቻላል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
5. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ ፖስታ አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
6. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ የድርጅቱ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ነው።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 /ሶስት/ ቀናት ውሰጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5(አምስት) ቀናት ውሰጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ለሚወዳደሩበት ሎት ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
8. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
9. 10ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
10. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
11. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
በስልክ ቁጥር 0114 71 40 06/ 0114 71 42 91 / 0114 71 43 58 መጠየቅ ይችላሉ።
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-29 12:00
- Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Menschen für Menschen Foundation (MfM)
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T08:14:24.000Z