Other Sales

አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት ሲጠቀምበት የነበሩትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በትምህርት፣ በጤና፣ በወጣት ልማት ዘርፍና በችግረኛ ቤተሰብ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ በመሰማራት ከተለያዩ መንግሥታዊ ሴክተር መ/ቤቶችና ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባባር በርካታ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ የሚገኝ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅታችን ሲጠቀምበት የነበሩትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም መግዛት የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07/ ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍለ-ሀገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት የሚሸጡትን ዕቃዎች ተመልክታችሁ የምትገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ ሞልታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል። ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ስምንተኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ የሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ይሆናል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ብዝቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ :-

ስልክ- 09 49 10 11 10 / 09 96 23 09 27

አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Integrated Development Association
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:38:07.000Z
← Back to all tenders