Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተርና ማረሻ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ የአቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ የእርሻ ትራከተር እና የእርሻ ማረሻ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእርሻ ትራክተርና ማረሻ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ለማከራየት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

 

የተከራዩ ስም

 

የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

 

የዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ

ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ሁኔታ

1

አቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናዜሽን አገልግሎት መስጫ

 

የእርሻ ትራክተር (በቁጥር 01) ብራንድ Massey Ferguson የስሪት ዘመን 2021 አቅም112HP እና ሞዴል MF6711

2.የእርሻ ማረሻ (በቁጥር 01) ብራንድ OTMA የስሪት ዘመን 2019 ሞዴል O/QD70/E

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት /ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው።

 

5,923,887.97

 

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት /ቤት ውስጥ ነው።

 

ጳጉሜ 04 ቀን 2018. 400 እስከ 600

 

ዝግ ጨረታ

 

የዝግ ጨረታው መመሪያ

1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፤ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፤ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪከት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዘበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።

2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፤ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ፤ በኢት/ያ ልማት ባንክ በሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

3. የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል።

4. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል። በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፤

5. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመከፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በሟሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽኔሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

6. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል።

7. የዝግ ጨረታ አሸናፊማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል።

8. የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ካለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፤የጉዞ ኢንሹራንስ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል።

9. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ጳጉሜ 04 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሎን ወርክአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል።

10. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 046-180-1528/38 ደውሎ ማነጋገር ይችላል።

11. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጨራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።

12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-09-09 12:00
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T10:55:45.000Z
← Back to all tenders