Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪ ከነጀነሬተሩ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሁለተኛ ዙር የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ መሐመድ ቦራ ለሰጠው የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪ ከነጀነሬተሩ ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሠረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሠጠው ስልጣን መሠረት በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

የሚሸጠው ንብረት

 

የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር

 

.

የንብረቱ አይነት

ብዛት

 

ንብረት የሚገኝበት ቦታ

 

ቀን

 

ሰዓት

 

ቦታ

 

1

Brade slicer

(01) set

 

 

 

 

 

 

 

በደ/// ቡርጂ ዞን፤ሶያማ ከተማ 02 ቀበሌ

 

 

 

 

 

 

 

 

7,237,089.33

 

 

 

 

 

 

 

 

መስከረም 12 ቀን 2019 .

 

 

 

 

 

 

 

 

4:00-6:00

 

 

 

 

 

 

 

በደ/ /ቡርጂዞን፤ ሶያማ ከተማ 02 ቀበሌ በአቶ ሞሃመድ ቦራ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል

 

2

Rotary oven

14Tray

3

Dough mixer

(01) set

4

Volumetric Dough Divider

(01) set

5

Molding Machine

(01) set

6

Flat tray with trolley

(02) set

7

French tray with trolley

(02) set

8

Diesel Generator 24kW

(01) set

 

ማሳሰቢያ፡-

1. ከላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች መግዛት የሚፈልግ ተደራዳሪ ተጫራች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25) በመቶ 1,809,272.33(አንድ ሚሊዩን ስምንት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ከ33/100) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላል።

2. ማሽነሪው የተተከለ ሲሆን የሚሸጠው ማሽኑ ብቻ በመሆኑ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ማሽነሪውን ነቅሎ የመውሰድ ሃላፊነት ያለበት ሲሆን የማሽነሪውን መንቀያ እና የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው ባሸናፊው ነው።

3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ስለሆነ ገዥው የቀረጥ ነጻ ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፤ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያውን ገዥው ይከፍላል

4. ሐራጁ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፤00-6፤00 ሰዓት ይከናወናል።

5. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ ለሚገዙ ባሸነፉት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው የህግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያ ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።

6. አሸናፊው የሐራጁ አሸናፊ መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ማሽነሪዎችን ለማስጠበቅ የሚከፈል ክፍያ ለማሸነሮዎች መጠለያ ኪራይ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎች የመክፈል ግዴታ አለበት።

7. አሸናፊው የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲን መስፈርት ካሟላ ሽያጩ በዱቤ ግዥ ይሆናል።

8. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15 ተከታታይ ቀናት ውስት አጠቃሎ መክፈል አለበት ካልከፈለ ባንኩ የሐራጅ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል። በድጋሚ ሲሸጥ የሚፈጠረውን የዋጋ ልዩነት ይከፍላል።

9. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኝበት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ንብረቶቹ በሚገኝበት ቡርጂ ዞን፤ ሶያማ ከተማ 02 ቀበሌ በአቶ ሞሃመድ ቦራ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ ሐራጁ በሚካሄድበት ቀን የሐራጁ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ማለትም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሐራጅ ቦታ በመገኝት ምዝገባ ማካሄድ ሲ.ፒ.ኦ እና የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ለጨረታው ኮሚቴ ማስረከብ አለበት።

10. ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪከት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-0606/03-03 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጐብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ካሉ ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።

11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-09-22 12:00
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T11:08:48.000Z
← Back to all tenders