Disposal Sale

ኤፍ ኤች ኢትዮጵያ ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃና መገልገያዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጀታችን

  • ኤፍ ኤች ኢትዮጵያ ያገለገሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  • የቢሮ ዕቃና መገልገያዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጀትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ /ብር ብቻ በመክፈል አዲስ አበባ፤ መገናኛ በተለምዶ 24 ቀበሌ 40/60 ቱሪስት ኮንዶሚኒይም አካባቢ በቅድስት ማሪያም ት/ቤት ገባ ብሎ በሚገኘዉ ዋናዉ የድርጅቱ መ/ቤት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ።
  2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ፣ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ (ሪሊት) በማሳየት፣ የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች፤ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎችን በአዳማ ከተማ ልዩ ስሙ “አመዲ ኪላ አካባቢ (ጨፌ ክፍለ ከተማ፣ ዳቤ ሶሎቂ ቀበሌ 13) ከዋናው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ዘወትር በሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡30 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት ተሸከራካሪም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን በጥቅል የሚያቀርቡበትን ዋጋ በዋና የጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው የመጨረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ፣ በጥቅል ለመለዋወጫና ለቢሮ ዕቃዎች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) በኤፍ ኤች ኢትዮጵያ (FH Ethiopia) ስም ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ከጨረታው ሰነድ ጋር ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን አሽናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ /ሲፒኦ/ታሳቢ ተደርጎለት ቀሪውን ገንዘብ አስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ ከፍሎ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለበት።
  6. የጨረታው አሽናፊ ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቱን ካልወሰደ፣ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል:: ሁለተኛ የወጣው ተጫራች አንደኛ በወጣው ተጫራች ዋጋ ለመውሰድ ፈቃደኛ ከሆነም ዕድሉ ይሰጠዋል።
  7. የጨረታው አሸናፊዎች ከከም ዝውውር ጋር የተያያዙትን ማንኛውንም ክፍያዎች ይከፈላሉ።
  8. ጨረታውን ያላሸነፈ ተጫራጮች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/የጨረታ አሸናፊው ከታወቀ በኃላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  10. ድርጅቱ ስለ ሽያጩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11.  ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 11 616 7092/ 09 59 32 09 27 በስራ ሰዓት ብቻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡ ኤፍ ኤች ኢትዮጵያ (FH Ethiopia) 

መገናኛ፤ በ40/60 ኮንዶሚኒየም አካባቢ ገባ ብሎ

ከገቢዎች ሚኒስቴር ፊት ለፊት

ከቅድስት ማርያም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎን

ፖ.ሳ.ቁ. 4181፤ ስልክ፡ +251116167092 ወይም +251959320927

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-08 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: FH Ethiopia
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T14:59:59.000Z
← Back to all tenders