Other Sales
ሕብረት ኢንሹራንስ በደንበኞቹ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸሙን ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የኩባንያው ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ አካል ቅሪቶችንና በባህር ጉዞ ጉዳት የደረሰባቸውን ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ሕብረት ኢንሹራንስ በደንበኞቹ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸሙን ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የኩባንያው ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ አካል ቅሪቶችንና በባህር ጉዞ ጉዳት የደረሰባቸውን ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ቁጥር 74
ክፍል 1 የተጫራቾች መመሪያ
1.1. ተጫራቾች ቃሊቲ ጃቲ ኪዳነ ምህረት ፊት ስፌት ዲ.ኤች.ገዳ ብርድልብስ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው የተጎዱ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ንብረቶች ማቆያ (ሪከቨሪ) ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም አስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት በመምጣት ተሽከርካሪዎችንና ሴሎች ንብረቶችን ማየት ይችላሉ።
1.2. ተጫራቾቾ ተሽከርካሪዎቹን ወደም ሴሎች ንብረቶችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ሰዓት ድረስ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
1.3. ተጫራቾች ለተሽከርካሪዎቹ በዚህ ጨረታ ሰነድ ክፍል ሁለት በተገለፀው መሠረት ሕብረት ኢንሹራንስ /Hiber Insurance/ ተብሎ በሲፒኦ የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ስተሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ ይመስስላቸዋል። አሸናፊዎች በጨረታ ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ የጨረታው ውጤት ከተገስፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል።
1.4. የጨረታ አሸናፊዎች የተሽከርካሪዎችን ወይም ሴሎች ንብረቶችን ሙሉ ክፍያ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ጨምረው ከከፈሉ በኋላ ተሽከርካሪዎችን ወይም ሌሎች ንብረቶችን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሸነፉትን ንብረት ከፍስ ካልወሰዱ ኩባንያው ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ከመሆኑም በላይ ንብረቶቹን ጨረታ በማውጣትም ሆነ ያስጨረታ የመሸጥ፣ የተሸmበትን ገንዘብ ስኩባንያው ገቢ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው:: በተጨማሪም ተጫራቾች ስጨረታው ያስያዙት ገንዘብ አይመስስላቸውም።
1.5. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር ከከፈሉ በኋላ በ10 የስራ ቀናት ስፕ ተሽከርካሪውን ወይም ንብረቶቹን የማያነሱ ከሆነ ኩባንያ ንብረቶቹ ለቆዩበትና ለተጠበቁበት ስእያንዳንዱ ቀን ብር200.00 (ሁለት መቶ ብር) ያስከፍላል።
1.6. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከ ተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈልግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙት አይጠየቁበትም። ተሽከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ በመንግስት የሚፈልግ የክፍያ ጥያቄ ቢኖር የመክፈል ኃላፊነቱ የገዥው ይሆናል።
1.7. ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን ኩባንያው ስገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሚወስነውን የቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍስጡ ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል።
1.8. ገዥዎች ተሽከርካሪዎችን ከገዙና ከተረከቡ በኋላ ከክልሎች የሚመጡ ፋይሎችና ክሊራንሶች ቢኖሩ ተከታትስጡ የሚያመጡት ገዢዎች ይሆናሉ።
1.9. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ከተረከቡ በኋላ በ6ወር ጊዜ ውስጥ የስም ዝውውር ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል። ከ6ወር በኋላ ከስም ዝውውር ጋር በተያያዘ ስሚቀርቡ ጥያቄዎችና ችግሮች ኩባንያው ሃላፊነት አይወስድም።
1.10. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥፕር ባስስልጣን የተሽከርካሪ አገልገሎት አሰጣጥና ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ስሰራር መመሪያ ቁጥር 19/2010 መሠረት በሚስወፕ ሻንሲ የተባሉ ተሽከርካሪዎች ሻንሲያቸው ካልተስወጠ ኩባንያችን ስም ማዘዋወር የማይችል መሆኑን እንገልፃስን።
1.11. ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወደም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል ኩባንያው የተሻስ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 16:30
- Bid opening: 2026-09-05 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Insurance Company S.C.
- Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T15:00:06.000Z