Other Sales
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤ.ቁ 1057 የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ ፊት ለፊት ወደ ችሎት አደባባይ በሚገነጠለው አስፋልት 70 ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው.ጽ/ቤታችን ከጠዋቱ 3፡00 –ቀኑ 1ዐ፡ዐዐ ሠዓት ድረስ በአካል ቀርበው ማመልከት ይቻላል፡
2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በዳሽን ባንክ ወይም በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ከ5 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መረጃ የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በፌዴሬሽናችን ጽ/ቤት በመቅረብ በአስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጐኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ ሁለተኛው አሸናፊ ራሱ ባሸነፈበት ዋጋ ከፍሎ እንዲገዛ ይደረጋል፡፡
7. ተጫራቾች የድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ጋር በመቅረብ የንብረቶቹን ሙሉ መረጃ የያዘ ሠነድ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 9 የሥራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 9 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከ6ኛ ቀን እስከ 9ኛው ቀን ደግሞ ንብረቶቹ በአካል የሚታዩበት ሲሆን በ9ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሠዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1553003 /0921 324330/0908569070
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ.)
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ9ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-09-02 16:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ9ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federation of Ethiopian Association of Persons with Disabilities (FENAPD)
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:26:07.000Z