Other Sales

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የንብረት ማስወገድ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራቾች ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች ለሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አሥር ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በአንድ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ በመስሪያ ቤቱ አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸናፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ንብረቶችን ማንሳት ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች በሌላው ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማስገባት አይችልም፡፡

6. ድርጅታችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-08-80-99 ወይም 0913-21-50-37

አድራሻ፡- 4 ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 50.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T09:21:03.000Z
← Back to all tenders