Other Sales
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ተሽከርካሪዎችና የተለወጡ የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ፀሐይ ኢንሹራንስ ኢማ
TSEHAY INSURANCE S.C
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተለወጡ የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተሽከርካሪዎችንና የተሽከርካሪ አካላትን፣ እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ ቃሊቲ መኮድ ፊትለፊት በሚገኘው የኩባንያዉ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ በቆሙበት ከነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመገኘትና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ የመነሻ ዋጋዉን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ለተሽከርካሪዎች ከብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) እንዲሁም የተሽከርካሪ አካላት ላይ ከብር 500.00(አምስት መቶ) ማነስ የለበትም።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
- በተሽከርካሪዎችና ሌሎች አካላት ላይ ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናል።
- በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
- የጨረታዉ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን መረከብ ዕቃዎቹንም ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለባቸዉ:: ይህ ካልሆነ ግን የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 111 97 71/70 ወይም 011 650 79 79 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰዉ ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-09-05 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsehay Insurance S.C.
- Bid bond: 10% ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ለተሽከርካሪዎች ከብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) እንዲሁም የተሽከርካሪ አካላት ላይ ከብር 500.00(አምስት መቶ) ማነስ የለበትም።
- Published on: Reporter (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T11:57:16.000Z