Other Sales
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ከግንባታ የተረፉ ቁርጥራጭ የብላክ ቴንትድ ላስትራ መስታወት፣ በገላን ጉራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚገኝ የአጠና እንጨት ባሉበት ሁኔታ እንዲሁም በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኝ ያገለገለ የፕላስቲክ የታሸገ ማጣበቂያ ኮላ እና ልዩ ልዩ ህትመት ሰነዶች መልሶ ለሚጠቀሙ (Re-cycle) ድርጅቶች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ
Other SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal Sale
Addis Ababa
More tags
Plastic Raw MaterialsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic ProductsPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksWood and Wood WorkingChemicals and ReagentsAmharic2merkatoAddis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት አያት አደባባይ በሚገኘው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አማካሪ ቢሮ የሚገኝ ከግንባታ የተረፉ ቁርጥራጭ የብላክ ቴንትድ ላስትራ መስታወት፣ በገላን ጉራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚገኝ የአጠና እንጨት ባሉበት ሁኔታ እንዲሁም በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኝ ያገለገለ የፕላስቲክ የታሸገ ማጣበቂያ ኮላ እና ልዩ ልዩ ህትመት ሰነዶች መልሶ ለሚጠቀሙ (Re-cycle) ድርጅቶች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች አቃቂ ቃሊቲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት በ CCRDA መስሪያ ቤት እና በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ገባ ብሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ኮንስትክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከርድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00( ሶስት መቶ ብር ከ00/100) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ (ከጠዋቱ 2፡00 – 11፡00)፣ ቅዳሜ ጨምሮ (ከጠዋቱ 2፡00-6፡00) በስራ ሰዓት ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ የአዲስ አበባ ኮንስትክሽን ዲዛይን ግንባታማማከር ድርጅት ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች በስራ ሰዓት ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ ጨረታ ማስከበሪያ 70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት በሲ.አር.ዲ.ኤ እና በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር: 0946463816/ 0912085572/0930489018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-18 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
- Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
- Bid bond: 70,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T12:59:36.000Z