Other Sales

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ዕቃ ግምጃ ቤት ተከማችተው የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ ግ/ጨ/012/2018

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ዕቃ ግምጃ ቤት ተከማችተው የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ሎት

 

የእቃው ዓይነት

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

1.

 

ያገለገሉ የተለያዩ ብረቶች እና ኬብሎች

 

ጳጉሜ 5 ቀን 2018 . 800 ሰዓት

ጳጉሜ 5 ቀን 2018 . 830 ሰዓት

ብር 50,000.00 (ሃምሳ ብር)

2.

 

ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ ጎማዎች

ጳጉሜ 5 ቀን 2018 . 800 ሰዓት

ጳጉሜ 5 ቀን 2018 . 830 ሰዓት

ብር 5.000.00 (አምስት ብር)

1. ማንኛውም የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የትኛውም አካል እና ማንኛውም የንግድ ፍቃድ የሌለው ግለሰብ የጨረታ ሰነድ ገዝቶ የጨረታ ዋስትና በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000149984384(EEU N/A/AR CU CON FOR EL CON) በሚለው ግቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

3. አድራሻ ፒያሳ አቡነጴጥሮስ ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-210 በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፣

4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ ግ/ጨ/12/2018. የሚል ምልክት በማድረግ ሎት-1 እና ሎት-2 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

6. የጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 84 82 00 07 መደወል ይችላሉ።

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-10 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopia Electric Utility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 400.00 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T13:29:49.000Z
← Back to all tenders