Other Sales
የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች፣ ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶችና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ዘርፋችን ሳሪስ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን
- ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣
- ንቃይ ቆርቆሮች፣ቁርጥራጭ
- የተሽከርካሪና ሌሎች
- ብረታ ብረቶችና
- የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 ብር አምስት መቶ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቃሊቲ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት 7፡30 1፡30 እና ቅዳሜ ከ3፡00 እስከ 6፡30 ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.አ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዘርፋችን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልፅ 15 % የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ማሳየት አለባቸው፡፡
- ጨረታው መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በ5 /አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በመከፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ከ5ኛው ቀን በኋላ ላላነሱበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው በራሱ ወጪ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ንቃይ ቆርቆሮች፣ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች፣ማንሳት ማስጫንና ማጓጓዝ ይኖርበታል፡፡
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0953845811 መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡ ቃሊቲ ቆርኪና ጣሳ ፋብሪካ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር : 0953845811
የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-09-15 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T08:54:31.000Z