Other Sales
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የቁም ደን መሸጥ ይፈልጋል
Description
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ወረዳ ቀረር የመንግስት ደን ውስጥ 2973.32 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን ፣ በደ/ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ እና ተሁለደሬ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች በተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 10,858.02 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ፣5.5 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ ቁም ዴን እና የወደቀና የደረቀ የፈ/ጽድ 322.98 ሜ/ኩብ በድምሩ 1,865 ሜ/ኩብ ፣ ደ/ጎንደር ዞን ገና በጌምድር፣ላ ጋይንት እና ደራ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 4047.7 ሜ/ኩብ የፈ/ፅድ፣ 23,870.16 ሜ/ኩብ ነጭ ባህር ዛፍ እና 60.83 ሜ/ ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን በድምሩ 27,978.69 ሜ/ኩብ ቁም ደን፤ በሰ/ሸዋ ዞን ባሶና ወረና ወረዳ ጎሺ : አገር : ቀበሌ አባሲ አገር የመንግስት ደን እና ጣርማ በር ወረዳ ደብር ማዕዛ ቀበሌ ደብረ ማዕዛ የመንግስት ደን ውስጥ የሚገኘውን 20,630,46 ሜ/ኩብ የነጭ ባህርዛፍ ፣465.59 ሜ/ኩብ የፈ/ፅድ እና 2998.85 ሜ/ኩብ ፓይነስ ፓቹላ ቁም ደን በድምሩ 24,094,9 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ VAT ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ለጨረታ የቀረበውን ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ስዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ዉስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ እ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ዉስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለትመቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርቶች በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸዉን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ደ ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች «የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጅ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊዉ ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
8. ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ክፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ።
10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 058 226 3095፣ደ/ታቦር 058 441 0306፤ደ/ብርሃን 011 637 5017፣ እንጅባራ 058 227 0485፣ ደ/ማርቆስ 058 8719 004፤ኮ/ቻ 0914 716 636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ዉስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ዉስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Forest Enterprise
- Buyer address: ባህር ዳር ቀበሌ 14 አረጋውያን ህንፃ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T08:56:55.000Z