Chemicals and Reagents

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከመስከረም 01 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚያመርተውን ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የተረፈ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከመስከረም 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት፡፡
  • ለተነጠረ ሞራ የጨረታ ማስከበሪያ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
  • አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
  • የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል፡፡
  • ጨረታው ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-08 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
  • Buyer TIN: 0000028921
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺ ብር)
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: 2merkato.com (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T09:11:40.000Z
  • Buyer website: https://www.aaae.gov.et/en/
← Back to all tenders