Disposal Sale
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-04/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
ቁርጥራጭ ብረቶች |
ኮተቤ መካኒካል ወርክሾፕ ግቢ ውስጥ |
ኪ.ግ |
32,120 |
60,000 |
መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡ዐዐ |
መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
|
2 |
15kV 3*95+25 ABC Cable |
ጎፋ ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት |
ኪ.ግ |
156,924 |
930,000 |
መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡ዐዐ |
መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
|
15KV 3*50+25 ABC Cable |
46,500 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲየን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን፣ ለብረታ ብረት ተጫራቾች የብረታ ብረት አቅላጭ መሆናቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ማስረጃ ማቅረብ እንዳለባቸው እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
4.ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር(Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
8. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፡፡
9. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ /ሊደረግ ይችላል፡፡
10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 0905 115 511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
12.ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር፡- 0111 119 897 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-18 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T10:04:41.000Z