Disposal Sale

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ. በዋናው መስሪያ ቤት ሲጠቀምባቸው የነበሩ በመጠኑ ያገለገሉ ተሽርካሪዎች እንዲሁም ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

HCSC/M/NCB/-0001/2018

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ በዋናው መስሪያ ቤት ሲጠቀምባቸው የነበሩ በመጠኑ

  • ያገለገሉ ተሽርካሪዎች እንዲሁም
  • ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል.

ስለሆነም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ የነዋሪነት መታወቂያ እንዲሁም ቋሚ አድራሻ ያላቸው ግለሰቦች እንዲሁም ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶቸ ሁሉ ለመሳተፍ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር(10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ወስጥ በተገለፀው አድራሻ በአካል በመገኘት የመኪኖቹን ይዞታ መመልከት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ የመነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 500 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃየተ/የግ/ማህበር 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
  4. ጨረታው መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 ታሽጎ በቀጣዩ ቀን መስከረም 09 ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  5. ተጫራቾች ስለጨረታ ሰነዱ አሞላል እንዲሁም ሌሎች ከጨረታው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠውን ዝርዝር በመከተል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጅምሮ እስከ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ከታች በተቀመጠው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ከተጠቀሰው ሰአት ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ጀርባ

ጌትአስ ኢንተርናሽናል ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ኢሜል፡ [email protected] /  [email protected]

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-09-19 09:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Habesha Cement Share Company
  • Buyer address: አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ ጌት-አስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T10:34:42.000Z
← Back to all tenders