Other Sales

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን 57 ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን፤ አንድ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ እና ሁለት ሞተር ሳይክል ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨርታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሣሪስ ሚችልኮትስ በሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን 57 ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን፤ አንድ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ እና ሁለት ሞተር ሳይክል ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨርታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ/ ብር በመክፈል ከጳጉሜ 02 ቀን 208 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ  ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እንዲሁም ከሠዓት ከቀነ 7፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋ/መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

3. አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡

5.. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

6, ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT) ማሳየት አለባቸው፡፡

7. ጨረታው መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

8. የከም ማዘዋወሪያና ተያያዥ ክፍያዎች በአሸናፊው ተጫራች የሚከፈል ይሆናል፡፡

9. አሸናፊው ተጫራች የመረከቢያ ሰነድ ወይም የሽያጭ ትዕዛዝ ደብዳቤ የሚሰጠው በጨረታ ላሸነፈበት መጠን በቅድሚያ ክፍያ ሲፈፅም ብቻ ነው፡፡

10. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፈርማ ማድረግ  ይጠበቅባቸዋል፡፡

11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፡፡

12. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በ5 /አምስት የሥራ  ቀናት በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ ከ15ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡

13. አሸናፊው በራሱ ወጪ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማስጫንና ማጓጓዝ አለበት፡፡

14. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንገድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ስፈት
ስልክ ቁጥር 0114-1634 83 አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-09-28 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Trading Businesses Corporation
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T07:39:48.000Z
← Back to all tenders