Fuel and Lubricants
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማታስወቂያ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች እና ለተሽከርካሪ መለዋወጫነትተገዝተው በሰቶር ተከማችተው የሚገኙ ልዩ ልዩ ስፔር ፓርቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶች
ሎት -1
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ምርምራ |
|
1 |
ያገለገሉ የተለያዩ የመኪና ሞዴሎች |
ቁጥር |
25 |
|
|
2 |
ያገለገሉ የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች |
ቁጥር |
363 |
|
|
3 |
ያገለገሉ የተለያዩ የተሽከርካሪ ባትሪዎች |
ቁጥር |
30 |
|
|
4 |
የተቃጠለ የሞተር ዘይት |
በሊትር |
1200ሊትር |
ከበርሜል ጋር |
|
5 |
ቁርጥራጭ ብረቶች |
በኪሎ |
1000ኪ.ግ |
ግምታዊ ተመን |
ሎት 2
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ምርምራ |
|
1 |
ጥቅም ላይ ያልዋሉ የመኪና መለዋወጫዎች |
በአይነት |
449 |
በእያንዳንዱ አይነት ውስጥ የተለያየ ብዛት አላቸው |
1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች (ግለሰብ ወይም ድርጅቶች) ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የቀበሌ (የፋይዳ) መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ድርጅት ከሆነ ደግሞ የድርጅቱን የውክልና ደብዳቤ ይዞ መቅረብ አለበት።
2. ተጫራቾች በሸጎሌ የ ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው ግዥ ዲፓርትመንት በመምጣት የሎት 1 ወይም የሎት 2 የተለያዩ ሰንዶች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 400 (አራትመቶ) ብር// ወይም ለሁለቱም ሰነዶች 800.00 (ስምንት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን በመግዛት ዘወትር በሥራ ቀናት ጠዋት 3፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡30-10፡00 ሰዓት እስከ 15 አስራምስተኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ሸጎሌ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት እና ዘነበ ወርቅ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ በመሄድ ንብረቶቹን በአካል መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለሚገዙዋቸው ለእያንዳንዱ ዕቃዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሣጥኑ ከመታሸጉ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
6. የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
7. አድራሻ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ከዌንጌት አደባባይ ከፍ ብሎ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል አጠገብ ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 011-517-25-21 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-21 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Broadcast Corporation
- Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ወይም ለሁለቱም ሰነዶች 800.00 (ስምንት መቶ) ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T07:52:54.000Z