Metal and Metal Working

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ሪከቨሪ የሚገኙ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት እና ኮንቴነሮችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ሪከቨሪ የሚገኙ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት እና ኮንቴነሮችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹንና የተሽከርካሪ አካላትን መግዛት ለሚፈልጉ ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ በሚገኘውየኩባንያችን ዋና መ/ቤት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ወይንም ቃሊቲ የኩባንያችን ሪከቨሪ ግቢ በመገኘት የተዘጋጀውን ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የሚገዙበት ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ እስከ መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ

  • ተጫራቾች ንብረቶችን እና ተሽከርካሪዎችን ቃለቲ ሸዋ ዳቦ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ከጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  • ጨረታው መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡30 ስዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የተገኙ ተጫራች ወይንም ተውዮች በተገኙበት ይከፈታል
  • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) በቡና ኢንሹራንስ ኢማ ወይም Buna Insurance S.C ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም።
  • ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታ በፊት አመታዊ የተሽከርካሪ ግብር እና ቅጣት ቢኖር በሻጭ የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ወጪ ያለ ዕዳ ካለ በኩባንያው ይሸፈናል። በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
  • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 የሥራ ቀን ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
  • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ.

ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት

ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ

- 911-99-31-15/0114626090 ሪከቨሪ

011-1-26-31-46/011-1-26-28-61


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-09-19 09:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bunna Insurance S.C.
  • Buyer TIN: 0038530762
  • Buyer address: ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 15% ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T15:36:24.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders