Other Sales
በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የቢቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ከቢቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የተሰበሰቡ የሚወገዱ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የቢቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ከቢቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የተሰበሰቡ የሚወገዱ የተለያዩ አሮጌ ብረታ ብረቶች በሽጭ ለማስወገድ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብሰበዉ ስለሚገኙ ጽ/ቤታችን አጥር ግቢ ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ አሮጌ ብረታ ብረቶች በተመን እንዲሸጥ ክልሉ በቁጥር አብክመ/ገቢ/188 በቀን 04-10-2017 በተጻፈ መመሪያ መሰረት ጽ/ቤቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡
1. የምትገዙበት ዋጋ ግልጽ አድርጎ በመፃፍ ፊርማና ስም በማስቀመጥ በፖስታ ታሽጎ ቢቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ /ቡድን ቢሮ ድረስ በመምጣት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለወጥ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉ ማግለል አይችሉም፡፡
3. መ/ቤቱ ካቀረበዉ መነሻ ዋጋ በታች የቀረበ የመወዳደሪያ ዋጋ ተቀባይነት የለዉም፡፡
4. አሸናፊዉ ያሸነፋቸዉን አሮጌ ብረታ ብረቶች በ5 የሥራ ቀናት ዉስጥ በራሱ ማንኛዉም ወጭ በመሸፈን ሊወስድ ነዉ፡፡
5. የጨረታ ማቅረቢያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚዉል ሲሆን በ16ኛዉ ቀን 3፡30 ይታሸጋል፡፡
6. ጨረታዉ የሚከፈተዉ በእለቱ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉን በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ የጨረታዉን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታዉ ሂደት በተላለፈዉ ዉሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታ መክፈቻ እሁድ ፣ቅዳሜ እና የህዝብ በዓል ቢሆን በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም (በሲፒኦ) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲወስዱ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ በተጨማሪም አንደኛዉ ተጫራች አሸንፎ አልወስድም ቢል የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ሁለተኛዉ ተጫራች በአንደኛዉ ባሸነፈበት ዋጋ መዉሰድ ይችላል፡፡
10. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸዉ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀዉ ሰነድ ነዉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የግዥ /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
11. በተጫራቾች የሚቀርበዉ መጫረቻ ሰነድ ላይ አሻሚ ነገሮች መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለዉ ፓራፍ ማድረግ አለባቸው፡፡
12. አሸናፊው የሚለየዉ በአንድ ኪ/ግ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበዉ ነዉ፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 665 05 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የቢቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚዉል ሲሆን በ16ኛዉ ቀን 3፡30
- Bid opening: 2026-09-22 12:00
- Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚዉል ሲሆን በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Bitchena Correctional Facility
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Be'kur (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T08:30:00.000Z
- Source: 2merkato