Other Sales
የአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት በ13/01/2019 ዓ/ም እና 16/01/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት፣ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የኢቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከሰ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅሰቃሴያቸውን ለታከሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣ በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 13/01/2019 ዓ/ም እና 16/01/2019 ባሉት ቀናት ለግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተቁ |
የጨረታ ቦታ
|
የጨረታ ዓይነት
|
ሰጨረታ የቀረቡ እቃዎች
|
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ቃሊቲ ጉምሩክ
|
ግልፅ እና ሃራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፤ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብ ነክ ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልፅ ጨረታ እስከ 13/01/19 ረቡዕ እና 16/01/2019 ቅዳሜ ጠዋት 3፡ 45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 4:45 |
ለግልፅ ጨረታ በ 13/01/2019 እና 16/1/2009 ጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00 |
5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፦ በቃሊቲ ጉ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውስው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-26
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-26 12:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Oromia
- Publishing entity: Awash Custom Commission Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 16, 2026)
- Posted at: 2026-09-16T08:30:24.000Z
- Source: 2merkato