Disposal Sale
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊያሟሉ የሚችሉ ፈላጊዎች መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤ በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ወንድ፤ ጋር ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ፣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፤ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው፤ ብር 500 (አምስት መቶ ብር)፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በከተማ አስተዳደሩ አካውንት ገቢ በማድረግ፤ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ፤ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ሥራ ቀናት ዉስጥ፣ በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ በሌሉበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን፤ የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን፣ በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የቃላት እና የቁጥር ልዩነቶች የሚያጋጥም ከሆነ፤ ቦጨረታ ሰነዱ ላይ ላለው በላይነት ይኖረዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ፤ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-29 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Command Bureau
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 17, 2026)
- Posted at: 2026-09-17T08:47:51.000Z
- Source: 2merkato