Metal and Metal Working

በድሬደዋ አስተዳደር ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል አዳዲስና ያገለገሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በድሬደዋ አስተዳደር ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሰንጠረዡ የተመለከቱትን አዳዲስና ያገለገሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋበዛል።

ተ.ቁ

የንብረት ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የዕቃዎቹ ሁኔታና የሚገኙበት ቦታ

1

ልዩ ልዩ ያገለገሉ ብረትና የብረት ዕቃዎችና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታ-ዕቃዎችና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታ-ብረቶች (Scrap meta))

ኪ.ግ.

 

ተመዝኖ

 

ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ

2

የተለያዩ ጎማዎች

በቁጥር

 

 

3

ልዩ ልዩ ያገለገሉ እንጨትና የእንጨት ዕቃዎችና ሌሎች ቁርጥራጭ እንጨቶች

ኪ.ግ.

ተመዝኖ

 

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ: -

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (አምስት መቶ ብር) ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 በመክፈል በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቁጥር 3 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ3:00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንብረት ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት በመምረጥ የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል ለይተው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ጽፈው ከፈረሙ በኋላ በኤንቬሎፕ አሽገው ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግንፋ አ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

5. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ን/ፋ/ አ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 ውስጥ ይከፈታል።

6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።

7. የጨረታ መገምገሚያ መስፈርት ከፍተኛ ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ናቸው።

8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖሩባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃውን በዐ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

10, ሆስፒታሉ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ለተጨማሪ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0251124968 /0912058798 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። ወይም ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግንፋአ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት ተገቢውን መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የድሬደዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-28 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Sabiyan General Hospital
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T08:58:34.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders