Other Sales
አልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ማዕከል ያገለገሉ የፈትል ክፍል ማሽኖችን፣ የሽመና ክፍል ማሽኖችና የጨርቅ ማቅለሚያ ማሽኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ማዕከል ያገለገሉ የፈትል ክፍል ማሽኖችን፣ የሽመና ክፍል ማሽኖችና የጨርቅ ማቅለሚያ ማሽኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ እየጠየቅን ለበለጠ ማብራሪያ ከታች በሚገኘው የስልክ አድራሻ በመጠየቅ መረዳት ይችላሉ።
|
የስራው አይነት |
የጨረታው ሰነድ ግዥና መመዝገቢያ ቀን |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ያገለገሉ ማሽኖች መሸጥ
|
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት
|
በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል። 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ሌላ በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። |
ስለሆነም፡-
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Number/ ቁጥር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ WAT/ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራቾች ያስገቡትን ዋጋ 10 ከመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በአልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ማዕከል (ADIC) ስም የተዘጋጀ በንግድ ባንክ በተመሰከረለት የባንክ ቼክ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ሰበታ ዲማ ከሚገኘው ድርጅታችን የፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፤
8. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ባይገኙ የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስ.ቁ፡- 09 93-90 10 16፣ 09 12-61 73 91
አልሳም ኃላ/የተ/የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-02 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Alsam PLC
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T08:07:44.000Z
- Source: 2merkato