Other Sales

የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን አጭር እና ረጃጅም ብረታ ብረቶች የቆርቆሮ ግንጣዮች በግልጽ በጨረታ አወዳደድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ASEZ 01/2019

የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን አጭር እና ረጃጅም ብረታብረቶች የቆርቆሮ ግንጣዮች በግልጽ በጨረታ አወዳደድሮ መሸጥ ይፈልጋል

ማንኛውም ተጫራች ከታች በመስፈርት ላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፤የዘመኑን ግብር የከፈለና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና በጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጸ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN NO) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በስራ ሰዓት መግዛት ይችላል፡፡

6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 7(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡

9. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ8 (ስምንት)ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ይከፈታል።

10. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በመክፈል አጭር እና ረጃጅም ብረታብረቶች የቆርቆሮ ግንጣዮች መረከብ ይኖርበታል፡፡

11. ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0222 129 757

የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 7(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ8 (ስምንት)ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-30 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 7(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ8 (ስምንት)ኛው የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T10:30:37.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders