Other Sales

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የጽ/ቤት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤ.ቁ1057 የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ ፊት ለፊት ወደ ችሎት አደባባይ በሚገነጠለው አስፋልት 70 ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሠዓት ድረስ በአካል ቀርበው ማመልከት ይቻላል።

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በዳሽን ባንክ ወይም በአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ከ5 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መረጃ የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ ፖስታ በፌዴሬሽናችን ጽ/ቤት በመቅረብ በአስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጐኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።

5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ።

6. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ ሁለተኛው አሸናፊ ራሱ ባሸነፈበት ዋጋ ከፍሎ እንዲገዛ ይደረጋል።

7. ተጫራቾች የድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ጋር በመቅረብ የንብረቶቹን ሙሉ መረጃ የያዘ ሠነድ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ።

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከ5ኛ ቀን እስከ 7ኛው ቀን ደግሞ ንብረቶቹ በአካል የሚታዩበት ሲሆን በ7ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሠዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

10.ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0111 553 003 / 0921 324 330 / 0908 569 070

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ.)


Tender details

  • Deadline: 2026-10-03
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-10-03 16:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federation of Ethiopian Association of Persons with Disabilities (FENAPD)
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T10:50:37.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders