Other Sales
ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና የብረት የውሃ ማጠራቀሚያ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና የብረት የውሃ ማጠራቀሚያ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሐግ/ ተሽጨ/ 02 /2019
ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተራ ቁጥር |
ለጨረታ የቀረቡት ተሽከርከሪዎች ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
ሎው ቤድ ተሳቢዎች ( low bed trailers) |
03 |
|
2 |
ኪያ ሬይኖ የጭነት ተሽከርካሪ (KIA RHINO CARGO TRUCK) 50 ኩንታል |
02 |
|
3 |
መርሰዲስ ከባድ ተሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ጋራዥ( MERCEDES TRUCK MOBILE Workshop) |
01 |
|
3 |
መርሰዲስ ከባድ ተሽከርካሪ መኪና ማንሻ (MERCEDES TRUCK ) |
01 |
|
3 |
መጅረስ የጭነት ተሽከርካሪ (MAJRUS CARGO TRUCK) |
01 |
|
4 |
ዴዉ ኖቨስ የውሃ ቦቴ (DAEWOO NOVUS WATER TANK)8000 ሊትር |
01 |
|
5 |
ሞሶ ዴው ( MUSSO DAEWOO 4 seater) |
02 |
|
5 |
ማህንድራ ቦሌሮ ፒክ አፕ(MAHINDRA pickup) |
02 |
|
7 |
የብረት የውሃ ማጠራቀሚያ ( metal water tanker) 3000 ሊትር |
36 |
1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች ሸገር ፣ ገላን ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ ልዩ ስሙ ሲዳ አዋሽ፣ ከኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት ነዳጅ ማደያ አጠገብ በሚገኘው ቤዛ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ከሰኞ -ቅዳሜ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር፤ 1000004330793 ገቢ በማድረግ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ፣ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፣ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 5058፣ ቦሌ ሚኒ አጠገብ በሚገኘው ሴቪታ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ደረሰኙን በማቅረብ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ ከመስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች አንድ እና ከዛ በላይ ተሸከርካሪ ተወዳድረዉ መግዛት ይችላሉ:: ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ እና ዕቃ በተናጠል በመሙላት ከ10% (አስር በመቶ) የጨረታና ውል ማስከበሪያ C.P.O. ጋር አያይዘዉ በሰም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፣ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 5058፣ ቦሌ ሚኒ አጠገብ ከሚገኘው ሴቪታ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይችላሉ።
4.ጨረታዉ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም ፣ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሴቪታ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።
5.ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ።
6.ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡ 0116 639191 EXI.257/260 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ።
ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-10-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-11-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ እና ዕቃ በተናጠል በመሙላት ከ10% (አስር በመቶ)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T12:10:43.000Z
- Source: Qelal Tenders