Other Sales

ሁዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግል ማህበር ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሁዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግል ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘረሩትን ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል በመሆኑ ፍላጐቱ ያላቸውና ህጋዊ መስፈርቱን የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

ተ.ቁ

የእቃው ዝርዝር

መለኪያ

1

ብርቱካናማ ቀለም ያለው ከግድግዳ ላይ የተነቀሉ እንጨት ላይ የተመታ አልሙኒዬም ኮምፖሳይት፤ የተቆራረጡና ፍርስራሽ አልሙኒዬሞች እና አሉሚኒዬም የአንፖል ማቀፊያዎች

በጥቅል

2

አሮጌ የእንጨት በሮች፤ የተቆራረጡ እንጨቶች

በጥቅል

3

አሮጌ የቀለም ቆርቆሮዎች

በጥቅል

4

ፒቪሲዎችና እና የኤሌክትሪክ ኮንዲዩቶች

በጥቅል

5

አሮጌ የተቆራረጡ ቆርቆሮዎችና እንጨት ላይ የተመቱ ቆርቆሮዎች

በጥቅል

  • ተጫራቾች መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 እንዲሁም ከ7፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ብቻ ንብረቶቹን ሳር ቤት በሚገኘው መሐመዲያ ኘሮጀክት ግቢ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ብስራተገብርኤል ወረድ ብሎ በሚገኘው ሎሊ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቀጥር 15 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር ከፍለው በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 ድረስ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በፊትም ሆነ በኋላም የሚመጣ ተጨራች አይስተናገድም።
  • ተጫራቾች ንብረቶቹን በሙሉ ወይንም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡ ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡30 ላይ ይከፈታል የአሸናፊዎቹን ዝርዝር በድርጅቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ይገለፃል።
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የሚገዙትን ዕቃ በጥቅል ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  • ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ 30,000 (ሰላሣ ሺ ብር) በድርጅቱ ስም በማሰራት ከሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ስፒኦ ብቻ ከሰነዱ ውጭ ማስገባት አይቻልም፣ እንዲሁም ስፒኦ ያልተያያዘለት ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣ ሲፒኦ ለሚጫረተው ጨረታ ማስከበሪያ እንጂ ከዋጋው ጋር የማይደመር መሆኑን እናሣውቃለን።
  •  አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በመክፈል ማሸነፉን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት ማንሳት ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ያላነሳ ተጫራች ያስያዘው ሲፒኦ ተመላሽ አይሆንለትም።
  • ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ሲፒኦ በቀጣዩ የስራ ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ከሒሳብ ክፍል በድርጅቱ ሥራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ካሸነፈው የዕቃዎች ዝርዝር የተወሰኑ ዕቃዎችን መርጦ በከፊል ለሚወስድ ተጫራች ያስያዘው የጨረታው ማስከበሪያ አይመለስም።
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ሁዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid opening: 2026-10-07 09:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Huda Real Estate P.L.C.
  • Bid bond: 30,000 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T13:17:52.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders