Other Sales
ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ የግል ማኅበር ኦርጅናል አዳዲስ የግሬደር፣ የዶዘር፣ የኤክስካቫተር፣ የገልባጭ ፎቶንና የሎውቤድ የገልባጭ ሲኖ እና የገልባጭ ጀሊዮን መለዋወጫዎች እና ያገለገለ ቀላል ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኦርጅናል አዳዲስ የግሬደር፣ የዶዘር፣ የኤክስካቫተር የገልባጭ ፎቶንና የሎውቤድ፤
የገልባጭ ሲኖ እና የገልባጭ ደሊዮን መለዋወጫዎች እና አንድ ያገለገለ ቀላል ተሽከርካሪ
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ የግል ማኅበር ኦርጅናል አዳዲስ የግሬደር፣ የዶዘር፤ የኤክስካቫተር፣የገልባጭ ፎቶንና የሎውቤድ የገልባጭ ሲኖ እና የገልባጭ ጀሊዮን መለዋወጫዎች እና ያገለገለ ቀላል ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለፈለገ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ መስከረም 19፣ 20፣ 21፣ 22፣ 25፣ 26፣ 27 እና 28 ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ከድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት እና የመለዋወጫዎቹን ሳምፕል ማየት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን።
በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች
- ንግድ ምዝገባ፣
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ማስረጃ፣
- በውክልና ከሆነ ውክልና እና መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ተብሎ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ9፡05 ሰዓት ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።
አሸናፊው ተጫራች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ገንዘብን ሙሉ በመሉ በመክፈል ንብረቱን መውሰድ ይኖርበታል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 83 93 29 96 / 09 83 77 28 45 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-08
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-10-08 15:05
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: N.F.A Business P.L.C
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T13:35:24.000Z
- Source: Qelal Tenders