Other Sales

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተለያዩ የፋብሪካ እና የአክለሪክ ብርድ ልብስ ተረፈ ምርት እና ቁርጥራጭ የግንባታ ግብአቶችን /ብረት እና ቆርቆሮ/ የዘንቢል ከረጢት መስሪያ ግብአቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተረፈ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተለያዩ የፋብሪካ እና የአክለሪክ ብርድ ልብስ ተረፈ ምርት እና ቁርጥራጭ የግንባታ ግብአቶችን / ብረት እና ቆርቆሮ / የዘንቢል ከረጢት መስሪያ ግብአቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ተረፈ ምርት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በዋናው መ/ቤት ቦሌ ስካይ ላይት ሆቴል አጠገብ ካለው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚሰጡትን የመወዳደሪያ ዋጋ በሚጫረቱት ተረፈ ምርት ትይዩ በሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ ብቻ ማስፈር አለባችሁ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ካስገቡት ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ / CPO / የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 – 10፡30 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኩባንያው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በ11 ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንዲከፈት ይደረጋል።

6. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በአስር ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ያሸነፉትን ተረፈ ምርት መረከብ አለባቸው።

  • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  • ለበለጠ መረጃ 0114- 34 26 76 ይደውሉ።

አድራሻ፡- ኬኬ ኃላ የተ/የግል ኩባንያ
ቦሌ ክ/ከተማ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00
  • Bid opening: 2026-10-07 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: KK Private Limited Company
  • Buyer address: ብሔራዊ አካባቢ ከቀድሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና፣ በወርቃማው ብሔራዊ ባንክ መሃከል ወደ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት በሚወስደው መንገድ
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T14:16:09.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders