Other Sales
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ደንብ ማስከበር አገልግሎት የተለያዩ የተወረሰ ንብረትና የመሳሰሉት በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሽያጭ መለያ ቁጥር 01/2019
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ደንብ ማስከበር አገልግሎት የተለያዩ የተወረሰ ንብረትና የመሳሰሉት በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡- ተጫራቾች ጨረታውን በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ማለትም ከ 20/01/2019 እስከ 22/01/2019 ዕለት አንስቶ /ተከታታይ ለ3/ሶስት የስራ ቀናት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ በሚገኘው አዲሱ ህንፃ በልደታ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 901 9ኛ ፎቅ ቢሮ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነዱን የተጫራች መመሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት እንዲያስችላችሁ የከፈሉበት ደረሰኝ በማሳየት እቃዎቹ ባሉበት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ በሚገኘው የክፍለ ከተማ አዲሱ ህንፃ ቅጥር ግቢ ቢሮ 901 9ኛ ፎቅ በመምጣት ስቶርና ላይ ግቢ ጎማ ቁጠባ ደንብ ማስከበር ቢሮ ስቶር እቃውን በስራ ቀንና በስራ ሰዓት በአካል ማየት ይችላሉ፡፡ ከቀን 20/01/2019 ጀምሮ እስከ ቀን 22/01/2019 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ጨረተውን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመጨረሻ በ23/01/2019 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ 9ኛ ፎቅ የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ብሄራዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
3. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ በገዙበት ሰነድ ውስጥ የእቃውን ዝርዝር በሚገልፅ ሰንጠረዥ ውስጥ ዋጋ በሚለው ቦታ የአንዱ ዋጋና አጠቃላይ ዋጋ እንዲሁም የግርጌ አጠቃላይ ድምር በአሃዝና በፊደል መሙላት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10 ፐርሰንት ሲፒኦ በመስሪያ ቤታችን ማለትም በልደታ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት ስም አሰርቶ ከመጫረቻው ሰነድ ጋር አያይዞ በፖስታ አሽጎ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ለተጫራቾች ሁሉንም የተወረሰ ንብረት በጥቅል ሁሉንም መውሰድ አለባቸው፡፡ በተናጠል መውሰድ አይቻልም፡፡
6. ተጫራቾች የከፍተኛው ጨረታ መነሻነት በተያዘው ዋጋ ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ አስፈፃሚው ከፍተኛውን ጨረታ ዋጋ ማለትም አጠቃላይ ድምር ከፍተኛ ዋጋ ይመርጣል፡፡
7. የዘገየ ጨረታ፤ የማይነበብ ፅሁፍ ወይም ስርዝ ድልዝ በጨረታ መክፈቻ ተቀባነት የለውም፡፡
8. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ያገለገሉ እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ካለበት ቦታ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሶስት ቀናት ማንሳትይጠበቅበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀናት አንስቶ ያላጠናቀቀ አሸናፊ ተጫራች በቀን ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) ይከፍላል፡፡ ከ5 ቀናት በላይ ከቆየ በመንግስት ይወረሳል፡፡
9. መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋ/ስ/አስ/ ጽ / ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን አድራሻ፡-ልደታ በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ከፍ ብሎ የሚገኘው የልደታ ክፍለ ከተማ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0118549984 መደወል ይችላሉ፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት ፑስ የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lideta Sub City Administration Office
- Buyer address: የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ወይም ዛጉዌ ህንፃ አጠገብ የሚገኘው የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 30, 2026)
- Posted at: 2026-09-30T09:14:24.000Z
- Source: Qelal Tenders