Plastic Products

የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሲገለገልባቸው የቆዩ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሚወገዱ ንብረቶች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ሀ/ኢ/ፓ/ሽ/አ/01/2019

የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሲገለገልባቸው የቆዩ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልለ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተረፈ ምርት እና ፕላስቲክ ምርቶችን የማንሳት እና የማስወገድ ስራ ላይ የተሰማሩ እና ዘርፍ ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ድርጅት

2. የጨረታውን ሰነድ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ተ.እ.ታ አካቶ በመከፈል ከሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾችን ከጨረታው መክፈቻ ዕለት አስቀድሞ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።

4. ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በዚህ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። 11ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር በሚቀጥለው የስራ ቀን ሂደቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል።

5. የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ (Envelope) በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስም የተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

7. አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጠው በ 10 ቀናት ውስጥ የንብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ንብረቱን ማንሳት ይጠበቅበታል።

8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

  • በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ቅ/ጽ/ቤት የአንድ ማዕከል ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01፣ ስልክ ቁጥር 0462120641

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በዚህ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-12 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በዚህ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Industrial Parks Development Corporation
  • Buyer address: Kebena, Infront of Kenya Embassy, Bishan-gari Building Procurement and Property Administration Directorate 2nd Floor
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 01, 2026)
  • Posted at: 2026-10-01T08:29:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders