Other Sales

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩኘ አባል የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች (Bitumen Barrel) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) ሽያጭ የጨረታ ሠነድ
የጨረታ ቁጥር -Disposal MIG -MCE 0001/2019

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩኘ  አባል የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች (Bitumen Barrel) ሣይዝ ባለ 60*70 የሆነ በቁጥር 10,000 /አስር ሺህ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች አዲስ አበባ፣ልደታ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 08 ከመካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ከኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቀጥሎ ባለው የኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው ህንፃ 1ኛ ፎቅ የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  2. በጨረታው ለመሣተፍ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሆን ይችላል። በጨረታ የሚሣተፈው ድርጅት ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅትና በበጀት ዓመቱ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰነድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ጥቅል የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel)ለጨረታ ያቀረቡትን ጥቅል ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/CPO/ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ አንብበው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እንዲያቀርቡ ይመከራሉ።
  5. ተጫራቾች ቃሊቲ አዲሱ ተርሚናል ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ፤
  6. ተጫራቾች  የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ መሰረት የሚገዙበትን ዋጋ ከቫት በፊት እና ቫትን ጨምሮ በመጥቀስ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰአት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ረፋድ 4፡00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያና ሲፒኦ በሰም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር  ይችላሉ። ጨረታው ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም  ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ጠዋት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል።
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት/አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ   ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ንብረቱን ማንሳት ሲኖርበት ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል።
  8. አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ/ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች (Bitumen Barrel) የመጫን የማጓጓዝ እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
  9. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል።
  10. ሻጭ ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።


አድራሻ፡-ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ  ኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ

ማሳሳቢያ፡

  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251 91 190 0960 /+251 09 19 48 77 62 ይጠቀሙ።
  • ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር     


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-12 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Midroc Construction Ethiopia P.L.C.
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T12:59:46.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders