Other Sales

የዘመን ኢንሹራንስ አ/ማ ኩባንያ የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቅሪቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የዘመን ኢንሹራንስ አ/ማ ኩባንያ የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቅሪቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተሸከርካሪዎቹን የተሸከርካሪ ቅሪት እንዲሁም ሌሎች ቅሪቶችን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቦሌ ኃይሌ እና ዓለም ህንጻ ሁለተኛ ወለል ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸዋ ዳቦ ወደ ቀኝ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው የተጎዱ ተሸከርካሪዎች ማቆያ (RICOVERY) ውስጥ በማየት ከመስከረም 24 ቀን 2019ዓ/ም እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 2.00 ሰዓት እስከ 6.00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት 7.00 ሠዓት እስከ 11.00 ሠዓት ድረስ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

1. ተጫራቾች ንብረቶችን እና ተሸከርካሪዎቹን ከመስከረም 24 ቀን 2019ዓ/ም እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ጊቢ ውስጥ በመገኘት ማየት ይቻላል።

2. ጨረታው ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4.00 ሠዓት ተዘግቶ በኩበንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 07 ቀን 2019ዓ/ም ከጠዋቱ 4.30 ሠዓት ላይ ይከፈታል።

3. ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር ፐርሰንት) ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ ወይም(ZEMEN INSURANCE S.C) ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ከቀረጥ ነጻ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሸከርካሪዎች የተሸከርካሪ አካላት ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፈናል:: በጨረታው ለተካተቱት ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።

6. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

7. የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) 15 % (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላል።

8. አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ሳይነጣጠሉ በአንድ ጊዜ ከፍለው በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን ከሪከቨሪ መረከብ ይኖርባቸዋል።

10.የጨረታው አሸናፊዎች የስም ዝውውር እስከ ስድስት ወር ድረስ ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ማንኛውም ጉዳይ (ችግር) ኩባንያው ኃላፊነት አይወስድም።

11.ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ፡- 09-44-17-36-73 ወይም 09-11-47-30-21 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ዘመን ኢንሹራንስ አ/ማ

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-17 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Insurance S.C.
  • Buyer TIN: 0056898819
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 04, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T13:04:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders