Other Sales

በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሞጃ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-17/2019 ጨረታ

በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተውና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም OIL FITER, HIK VI- SION SOLID STATE DRIVES, HDD SEAGATE & COMPUTER RAM, DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER, AUTOMATIC VOLTAGE REGULATOR, COMPLETE SET DOUBLE LEAF STEEL FIRE RATED DOOR, LABORATORY STOOL CHAIR, የተለያዩ አልባሳት ሽቶዎች፣ ጫማዎች፣ የጸጉር ማሽን እና ሌሎች እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል።

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ - ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300.000.00 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች በወረቀት የሚያስይዙ ከሆነ የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPAN CUS- IOMS COMMISSION MODO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።

4. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም ( auction.et ) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስክሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

7. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (እምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. በተራ ቁጥር 07 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

9. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55 11/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ወይም 022-236-0190 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉ/ቅ/ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ
  • Bid opening: 2026-10-12 11:00
  • Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T07:43:53.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders