Other Sales
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሶሳ ዲስትሪክት ለወተት ማቀነባበሪያ እና ከብት እርባታ ፕሮጀክት ለብድሩ አመላለስ ዋስትና በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የመጀመሪያ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሶሳ ዲስትሪክት ለወተት ማቀነባበሪያ እና ከብት እርባታ ፕሮጀክት ለሰጠው ብድር ተበዳሪው በብድር ውሉ መሰረት የብድሩን ገንዘብ ሊመልሱ ባለመቻላቸው ለብድሩ አመላለስ ዋስትና በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና ከ1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ/Cash/ ወይም በከፊል ብድር መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ቀጥሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በነጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት በሚከተሉት ዝርዝር ጉዳዮች መሰረት መጫረት የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
|
ተ.ቁ.
|
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የሚሸጠው ንብረት ዝርዝር መግለጫ |
ሐራጁ የሚካሄድበት |
የሐራጅ ደረጃ
|
||||||
|
የንብረቱ አይነት |
የሚገኝበት አድራሻ |
ብዛት
|
የንብረቱ ግምት በብር |
የሐራጁ መነሻ ዋጋ |
ቦታ |
ቀን
|
ሰዓት
|
||||
|
1 |
መስፍን ታደሰ የወተት ማቀነባበሪያ ፕሮጀክት
|
መስፍን ታደሰ የወተት ማቀነባበሪያ ፕሮጀክት
|
የወተት ማቀነባበሪያ ማሽነሪዎች (አዲስ ወይም አገልግሎት ያልሰጡ) |
ም/ወለጋ፣ ነጆ
|
|
22,132,881.65
|
77,084,951.06
|
ነጆ ቅርንጫፍ
|
ጥቅምት 25/2019 ዓ/ም
|
ከጠዋቱ 4:00-6: 00 ሰዓት
|
1ኛ ደረጃ
|
|
ጀነሬተር |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
1 |
2,139,674.48 |
||||||||
|
ትራንስፎርመር (3 phase) |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
1 |
1,392,808.41
|
||||||||
|
ቶዮታ ፒክ አፕ ደብል ጋቢና /የስሪት ዘመን 2016 |
አዲስ አበባ |
1 |
4,245,495.56
|
||||||||
|
ኤፍ ኤስ አር (ደረቅ የጭነት) የስሪት ዘመን 2019 |
ም/ወለጋ፣ ነጆ
|
1 |
6,214,440.03
|
||||||||
|
ኤይ ሱዙ NPR (ባለፍሪጅ) የስሪት ዘመን 2015 |
ም/ወለጋ፣ ነጆ
|
1 |
6,424,105.12
|
||||||||
|
ትራክተር (የስሪት ዘመን 2016) |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
1 |
1,378,763.02
|
||||||||
|
ሞተር ሳይክሎች |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
3 |
264,233.57 |
||||||||
|
የቢሮ ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
|
131,217.97
|
||||||||
|
የውሃ ፓምፕ |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
5 |
218,188.20 |
||||||||
|
PVC የውሃ ታንከር |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
3 |
38,300.00 |
||||||||
|
የውሃ ቧንቧ |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
2 |
11,971.70 |
||||||||
|
የግንባታ ሥራዎች |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
|
25,702,313.26 |
||||||||
|
የወተት ላሞች/ሌሎች ከብቶችን ጨምሮ |
ም/ወለጋ፣ ነጆ
|
76 |
4,845,800 |
||||||||
|
የ40.6 ሄክታር የመሬት ልማት |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
|
403,737.97 |
||||||||
|
በፕሮጀክቱ ውስጥ የለሙ የዛፎች ግምት |
ም/ወለጋ፣ ነጆ |
|
1,541,020.12
|
||||||||
የጨረታ መመሪያ
- የሐራጁ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) ወይም 25% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ(cpo) በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች ከድርጅቱ የተሠጠውን ውክልና ደብዳቤ እና ማንነቱን የሚገልጽ የፋይዳ ማታወቂያ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ አሸናፊው 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ክፍሎ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ከፍያው በተሰጠው የቀን ገደብ ውስጥ ካልተከፈለ ግን ለሐራጁ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ እንዲወጣ ይደረጋል።
- ማሽነሪዎቹ ተሽከርካሪዎቹ የገቡት ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት በጨረታው ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ, ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ በአሸነፈው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያን ይከፍላል።
- ባንኩ ለሽያጭ ያቀረባቸውን ንብረቶች ለመሸጥ ቅድሚያ የሚሰጠው በካሽ ነው። ይሁን እንጂ የባንኩን የብድር መስፈርት ለሚያሟላ ተወዳዳሪ በከፊል ብድር ሊሸጥ ይችላል።
- ንብረቶቹን ከጨረታው በፊት ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከባንኩ ጋር ፕሮግራም በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለማንኛውም ተጨማሪ መረጃ ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሶሳ ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር -057-275-5554 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሶሳ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-11-04 12:00
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T08:25:21.000Z
- Source: Qelal Tenders