Other Sales

በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ
ቁጥር ግ09/2019 ዓ.ም

በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 160/201 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተውና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም SCHOOL & TRAV- ELLING BAGS፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፤ ሽቶዎች፣ ፔርሙዝ እና ሌሎች እቃዎች፣ SPRING LOCK, HNGES SET COMPLETE, ALUMINIUM SCRAP & TOP WINDOW HOLDING ARMS WITH COMPLETE SCREWS POLYESTER FUR JACKET & ECOLOGIC COFFEE WET MILL እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን: ጀምሮ: ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፤ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግባት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይችላሉ።

2. የጨረታ ሰነዱን ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም |ድረገፅ| ኦንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

3. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በ ETHIOPlAN CUSTOMS COMMSSON MODJOBRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተዉ ኦክሽን ኢትዮጵያ ሂደዉ በማስያዝ ወይም በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች ኦንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም። በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፤ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።

6. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethio pia] ብለው በማውረድ ወይም (auction.et] ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

7. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5፡00 ድረስ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት ኦንላይን መከታተል ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

9. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፣ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

10. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

11. በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

12. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

13. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው። በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም።

14. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/ 011 666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 /022-236-0190 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-13
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5፡00
  • Bid opening: 2026-10-13 17:00
  • Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5፡00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 5%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 06, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T09:05:53.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders