Other Sales
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-18/2019
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሠረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተዉ የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም ac adaptor, hd tv cable, tv wall-mount, led highboy light, skmei iron adult hand watch, wooden door frame & water purifier, out door solar straight light & straight light stand, led string lights, rubber nail filter, s/s manicure, metal decorative & eye lash, photo copy machine and printer, adult fabric cap, shopping bag & others, rechargeable camping portable shower, wall transformer, chemical mixing tank, channel steel, galvanized steel pipe, Heald frame, fabric micro fiber cleaning towel, single, double port face plate & & & other, s/s artificial earring & bearing, school bag, fabric adult cap & supermarket shelf, children sport shoes brand & lady sport shoes brand, lady skirt, lady tight & other, vibration analysis of center fugal blower fan, mobile screen protection glass electric crane scale hair clipper, perfume & trouser, touch screen oca glass m-triangle lcd screen defoaming machine with bubble remover & others, two side coated art paper, የስቴሽነሪና ማስታወቂያ እቃዎችና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሥራ ሰዓት ማየት ይቻላል።
2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር መሆኑን እናሳውቃለን።
4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ በኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች በወረቀት የሚያስይዙ ከሆነ የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
5. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ንሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
8. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
9. በተራ ቁጥር 07 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55 11/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ወይም 022-236 0190 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-19 10:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T07:44:18.000Z
- Source: Qelal Tenders